1 የእግዚአብሔር ልጅ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ።
2 በነቢዩ በኢሳይያስ፣ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፤“እነሆ መንገድህን የሚያዘጋጅ መልእክተኛዬንበፊትህ እልካለሁ፤
3 ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በበረሓ የሚጮኽ ድምፅ’።”
4 ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስ በበረሓ እያጠመቀና ለኀጢአት ስርየት የንስሓ ጥምቀት እየሰበከ መጣ።
5 የይሁዳ አገር በሞላ፣ የኢየሩሳሌም ሰዎች በጠቅላላ ወደ እርሱ በመሄድ ኀጢአታቸውን እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ተጠመቁ።