36 ስምዖንና ባልደረቦቹም ተከትለው ይፈልጉት ጀመር፤
37 ባገኙትም ጊዜ፣ “ሰዉ ሁሉ ይፈልግሃል” አሉት።
38 እርሱም፣ “ከዚህ ተነሥተን በአቅራቢያ ወዳሉት መንደሮች እንሂድ፤ እዚያም ልስበክ፤ የመጣሁት ለዚሁ ነውና” አላቸው።
39 ስለዚህ ወደ ምኵራባቸው እየገባ በመስበክና አጋንንትን በማስወጣት በመላዋ ገሊላ ይዘዋወር ጀመር።
40 አንድ ለምጻም ወደ እርሱ ቀርቦ ከፊቱ በመንበርከክ፣ “ብትፈቅድ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” በማለት ለመነው።
41 ኢየሱስም ለሰውየው በመራራት እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፣ “እፈቅዳለሁ፣ ንጻ” አለው።
42 እርሱም ወዲያው ከለምጹ ነጻ፤ ከበሽታውም ተፈወሰ።