4 ደቀ መዛሙርቱም መልሰው፣ “በዚህ ምድረ በዳ እነዚህን ለመመገብ የሚያስችል እንጀራ ከወዴት ይገኛል?” አሉት።
5 እርሱም፣ “ስንት እንጀራ አላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው።እነርሱም፣ “ሰባት” አሉት።
6 እርሱም፣ መሬት ላይ እንዲቀመጡ ሕዝቡን አዘዘ፤ ሰባቱን እንጀራ ይዞ ካመሰገነ በኋላ ቈርሶ ለሰዎቹ እንዲያድሉ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ እነርሱም ለሕዝቡ አደሉት።
7 እንዲሁም ትንንሽ ዓሣዎች ነበሯቸው፤ እርሱም ዓሣዎቹን ባርኮ እንዲያድሏቸው አዘዘ።
8 ሕዝቡም በልተው ጠገቡ፤ ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ የተረፈውን ቍርስራሽ ሰባት መሶብ ሙሉ አነሡ።
9 በዚያም አራት ሺህ ያህል ሰዎች ነበሩ፤ ካሰናበታቸውም በኋላ፣
10 ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ዳልማኑታ ወደተባለ ስፍራ ሄደ።