1 በዚያን ጊዜ የአራተኛው ክፍል ገዥ የነበረው፣ ሄሮድስ ስለ ኢየሱስ ዝና ሰማ፤
2 ባለሟሎቹንም፣ “እንዲህ ከሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ከሞት ተነሥቶ መጥቶአል ማለት ነው፤ ይህ ሁሉ ድንቅ ታምራት በእርሱ የሚደረገውም ለዚህ ነው” አላቸው።
3 ቀደም ሲል ሄሮድስ፣ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ ወህኒ አስገብቶት ነበር።
4 ምክንያቱም ዮሐንስ፣ “እርሷን እንድታገባ ሕግ አይፈቅድልህም” ይለው ነበር።
5 ሄሮድስም ዮሐንስን ሊገድለው ፈልጎ፣ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ይመለከተው ስለ ነበር ፈራ።
6 ሄሮድስ የልደቱን ቀን ሲያከብር፣ የሄሮድያዳ ልጅ በዘፈን ደስ ስላሰኘችው፣