28 “ያ አገልጋይ ከጌታው ፊት እንደ ወጣ አንድ መቶ ዲናር የእርሱ ዕዳ ያለበትን አገልጋይ ባልንጀራውን አግኝቶ እንቅ አድርጎ በመያዝ፣ ‘ያለብህን ዕዳ ክፈለኝ!’ አለው።
29 “ባልንጀራው አገልጋይም ከፊቱ ወድቆ፣ ‘ታገሠኝ እከፍልሃለሁ’ ብሎ ለመነው።
30 “ነገር ግን ሊታገሠው ፈቃደኛ ስላልነበረ፣ ያለበትን ዕዳ እስኪከፍለው ድረስ ወህኒ ቤት አስገባው።
31 የሆነውን ነገር ያዩ ሌሎች አገልጋዮችም በጣም አዘኑ፤ ሄደውም ሁኔታውን በሙሉ ለጌታቸው ነገሩት።
32 “በዚህ ጊዜ ጌታው አገልጋዩን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ ‘አንተ ክፉ አገልጋይ፤ ስለ ለመንኸኝ ያን ሁሉ ዕዳ ተውሁልህ፤
33 እኔ እንደ ማርሁህ አንተም ባልንጀራህን ልትምረው አይገባህም ነበርን?’
34 በቍጣም ያለበትን ዕዳ ከፍሎ እስኪጨርስ ድረስ ለአሳሪዎች አሳልፎ ሰጠው።