1 ስለዚህ ከሰማነው ነገር ስተን እንዳንወድቅ፣ ለሰማነው ነገር አብልጠን ልንጠነቀቅ ይገባናል።
2 ምክንያቱም በመላእክት በኩል የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነና ማንኛውም መተላለፍና አለመታዘዝ ተገቢውን ቅጣት ከተቀበለ፣
3 እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ ድነት ቸል ብንል እንዴት ልናመልጥ እንችላለን? ይህ ድነት በመጀመሪያ በጌታ ተነገረ፤ ከእርሱ የሰሙትም ለእኛ አረጋገጡልን።
4 እግዚአብሔርም በምልክት፣ በድንቅና በልዩ ልዩ ታምራት እንዲሁም እንደ ፈቃዱ በታደሉት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ስለ ዚሁ ነገር መስክሮአል።
5 ይህን የምንናገርለትን መጪውን ዓለም ለመላእክት አላስገዛም፤
6 ነገር ግን አንዱ በሌላ ስፍራ እንዲህ ብሎ መስክሮአል፤“ታስታውሰው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?ታስብለትስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው”