ዕብራውያን 2:4-10 NASV

4 እግዚአብሔርም በምልክት፣ በድንቅና በልዩ ልዩ ታምራት እንዲሁም እንደ ፈቃዱ በታደሉት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ስለ ዚሁ ነገር መስክሮአል።

5 ይህን የምንናገርለትን መጪውን ዓለም ለመላእክት አላስገዛም፤

6 ነገር ግን አንዱ በሌላ ስፍራ እንዲህ ብሎ መስክሮአል፤“ታስታውሰው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?ታስብለትስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው”

7 ከመላእክት ጥቂት አሳነስኸው፤የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንህለት፤

8 ሁሉንም ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት።እግዚአብሔር ሁሉን ከበታቹ ሲያስገዛለት፣ ያላ ስገዛለት ምንም ነገር የለም፤ ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ነገር ተገዝቶለት አናይም።

9 ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ ከመላእክት ጥቂት እንዲያንስ ተደርጎ የነበረው ኢየሱስ፣ የሞትን መከራ በመቀበሉ አሁን የክብርና የምስጋና ዘውድ ተጭኖለት እናየዋለን።

10 ሁሉ ነገር ለእርሱና በእርሱ የሚኖር እግዚአብሔር፣ ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ለማምጣት፣ የድነታቸውን መሥራች በመከራ ፍጹም ሊያደርገው የተገባ ነበር።