6 በዚህ ምክንያት መንገዷን በእሾህ እዘጋለሁ፤መውጫ መንገድ እንዳታገኝም ዙሪያዋን በግንብ አጥራለሁ።
7 ውሽሞቿን ተከትላ ትሄዳለች፤ ነገር ግን አትደርስባቸውም፤ትፈልጋቸዋለች፤ ሆኖም አታገኛቸውም።ከዚያም እንዲህ ትላለች፤‘ወደ ቀድሞ ባሌ እመለሳለሁ፤የፊተኛው ኑሮዬ ከአሁኑ ይሻለኛልና።’
8 እርሷም እህል፣ ዘይትና አዲስ የወይን ጠጅ የሰጠኋት፣ለበኣል አምልኮ ያደረጉትን፣ብርንና ወርቅን ያበዛሁላት፣እኔ እንደሆንሁ አላወቀችም።
9 “ስለዚህ እህሌን በመከር ጊዜ፣አዲሱም የወይን ጠጅ በደረሰ ጊዜ እወስዳለሁ፤ዕርቃኗንም እንዳትሸፍንበት፣ሱፍና የሐር ልብሴን መልሼ እወስድባታለሁ።
10 አሁንም በውሽሞቿ ፊት፣ነውሯን እገልጣለሁ፤ከእጄም የሚያድናት የለም።
11 የደስታ በዓሎቿን ሁሉ፣የዓመት በዓሎቿንና፣ የወር መባቻዎቿንሰንበቶቿንና የተመረጡ በዓሎቿን ሁሉ አስቀራለሁ።
12 ከውሽሞቼ የተቀበልሁት ዋጋ ነው የምትለውን፤የወይን ተክሎቿንና የበለስ ዛፎቿን አጠፋለሁ፤ጫካ አደርገዋለሁ፤የዱር አራዊትም ይበሉታል።