3 ከንጉሥ ፊት ተጣድፈህ አትውጣ፤ የወደደውንም ማድረግ ስለሚችል ለጥፋት አትሰለፍ።
4 የንጉሥ ቃል የበላይ ስለ ሆነ እርሱን፣ “ምን ታደርጋለህ?” ማን ሊለው ይችላል?
5 እርሱን የሚታዘዝ ሁሉ አይጐዳም፤ጥበበኛም ልብ ትክክለኛውን ጊዜና ተገቢውን አሠራር ያውቃል።
6 የሰው መከራ እጅግ ቢጫነውም፣ለሁሉም ነገር ትክክለኛ ጊዜና ተገቢ አሠራር አለው።
7 ሰው የወደ ፊቱን ስለማያውቅ፣ሊመጣ ያለውን ማን ሊነግረው ይችላል?
8 ሰው ነፋስን መቈጣጠር አይችልም፤በዕለተ ሞቱም ላይ ሥልጣን ያለው ማንም የለም፤በጦርነት ጊዜ ማንም ከግዴታ ነጻ እንደማይሆን፣ክፋትም የሚለማመዷትን አትለቃቸውም።
9 ከፀሓይ በታች የተሠራውን ሁሉ በአእምሮዬ መርምሬ፣ ይህን ሁሉ አየሁ። ሰው ሰውን ለመጒዳት ገዥ የሚሆንበት ጊዜ አለ።