መክብብ 11 NASV

እንጀራ በውሃ ላይ

1 እንጀራህን በውሃ ላይ ጣል፤ከብዙ ቀን በኋላ መልሰህ ታገኘዋለህና።

2 ሀብትህን ሰባት ቦታ፣ እንዲያውም ስምንት ቦታ ከፍለህ አስቀምጥ፤በምድሪቱ ላይ የሚመጣውን ጥፋት አታውቅምና።

3 ደመናት ውሃ ካዘሉ፣በምድር ላይ ዝናብን ያዘንባሉ፤ዛፍ ወደ ደቡብም ሆነ ወደ ሰሜን ቢወድቅ፣በወደቀበት ቦታ በዚያ ይጋደማል።

4 ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፤ደመናትንም የሚያይ አያጭድም።

5 የነፋስን መንገድ እንደማታውቅ፣ሕይወት ወይም መንፈስ በእናት ማሕፀን ውስጥ ወደሚገኘው አካል እንዴት እንደሚገባም እንደማታውቅ ሁሉ፣ሁሉን ሠሪ የሆነውን፣ የእግዚአብሔርን ሥራማስተዋል አትችልም።

6 ጠዋት ላይ ዘርህን ዝራ፤ማታም ላይ እጅህ ሥራ አይፍታ፤ይህ ወይም ያ፣ወይም ሁለቱ መልካም ይሁኑ፣የቱ እንደሚያፈራ አታውቅምና።

ወጣት ሳለህ ፈጣሪህን አስብ

7 ብርሃን መልካም ነው፤ፀሓይንም ማየት ለዐይን ደስ ያሰኛል።

8 ሰው ምንም ያህል ብዙ ዓመት ቢኖር፣በእነዚህ ሁሉ ይደሰት፤ነገር ግን ጨለማዎቹንም ቀናት ያስብ፤እነርሱ ይበዛሉና፤የሚመጣውም ነገር ሁሉ ከንቱ ነው።

9 አንተ ወጣት በወጣትነትህ ጊዜ ደስ ይበልህ፤በወጣትነትህም ዘመን ልብህ ደስ ያሰኝህ፤የልብህን መንገድ፣ዐይንህ የሚያየውንም ሁሉ ተከተል፤ነገር ግን ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ፣እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።

ምዕራፎች

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12