2 ተነሥቼ ወደ ከተማዪቱ እወጣለሁ፤በዋና ዋና መንገዶችና በአደባባዮች እዘዋወራለሁ፤ውዴንም እፈልገዋለሁ፤ስለዚህም ፈለግሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም።
3 በከተማዪቱ ውስጥ ሲዘዋወሩ፣የከተማዪቱ ጠባቂዎች አገኙኝ፤እኔም፣ “ውዴን አይታችኋል?”አልኋቸው።
4 ከእነርሱ ጥቂት ዕልፍ እንዳልሁ፣ውዴን አገኘሁት፤ ያዝሁት፤ወደ እናቴ ቤት እስካመጣው፣በማሕፀን ወደ ተሸከመችኝም ዕልፍኝእስካገባው ድረስ አልለቀውም።
5 እናንት የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፤ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት፣በሚዳቋና በሜዳ ዋልያ አማጥናችኋለሁ።
6 ከከርቤና ከዕጣን፣ከነጋዴም ቅመማ ቅመም ሁሉ በተዘጋጀ ሽቱ፣መዐዛዋ የሚያውድ፣እንደ ጢስ ዐምድ ከምድረ በዳ የምትዋጣው ይህች ማን ናት?
7 እነሆ፤ የሰሎሞን ሠረገላበታዋቂዎቹ የእስራኤል መኳንንት፣ሥልሳ ጦረኞች ታጅባለች፤
8 ሁሉም ሰይፍ የታጠቁ፣ሁሉም በጦርነት የተፈተኑ ናቸው፤የሌሊት አደጋን ለመከላከልም፣እያንዳንዳቸው ሰይፋቸውን በወገባቸው ታጥቀዋል።