1 እኅቴ ሙሽራዬ፣ ወደ አትክልት ቦታዬ መጥቻለሁ፤ከርቤዬን ከቅመሜ ጋር ሰብስቤአለሁ፤የማር እንጀራዬን ከነወለላው በልቻለሁ፤ወይኔንና ወተቴንም ጠጥቻለሁ።ወዳጆች ሆይ፤ ብሉ፤ ጠጡ፤እናንት ፍቅረኞች ሆይ፤ እስክትረኩ ጠጡ።
2 እኔ ተኝቻለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቶአል፤ስሙ! ውዴ በር ያንኳኳል፤ እንዲህ ይላል፤“እኅቴ ወዳጄ፣ ርግቤ፣አንቺ እንከን የሌለብሽ፤ ክፈቺልኝ፤ራሴ በጤዛ፣ጠጒሬም በሌሊቱ ርጥበት ረስርሶአል።”
3 ቀሚሴን አውልቄአለሁ፤ታዲያ እንዴት እንደ ገና ልልበስ?እግሬን ታጥቤአለሁ፤እንዴት እንደ ገና ላቈሽሸው?
4 ውዴ እጁን በበሩ ቀዳዳ አሾለከ፤ልቤም ስለ እርሱ ይታወክ ጀመር።