63 አገረ ገዡም በኡሪምና በቱሚም እግዚአብሔርን የሚጠይቅ ካህን እስኪነሣ ድረስ፣ እጅግ ከተቀደሰው ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው።
64 ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ብዛት 42,360 ነበረ፤
65 ይህም 7,337 ከሚሆኑት ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻቸው በተጨማሪ ነው፤ 200 ወንድና ሴት ዘማሪዎችም ነበሯቸው።
66 736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች፣
67 435 ግመሎችና 6,720 አህዮች ነበሯቸው።
68 በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት በደረሱ ጊዜ፣ አንዳንድ የቤተ ሰብ መሪዎች በቀድሞው ቦታ እንደ ገና ለሚሠራው የእግዚአብሔር ቤት በበጎ ፈቃድ ስጦታ አደረጉ።
69 እንደየችሎታቸውም 61,000 የወርቅ ዳሪክ፣ 5,000 ምናን ብር፣ 100 ልብሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጡ።