1 ዳዊት በቤተ መንግሥቱ ተደላድሎ በተቀመጠበት ጊዜ፣ ነቢዩ ናታንን “እነሆ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል” አለው።
2 ናታንም ለዳዊት፣ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለ ሆነ፣ ያሰብከውን ሁሉ አድርግ” ሲል መለሰለት።
3 በዚያም ሌሊት የእግዚአብሔር ቃል ወደ ናታን መጥቶ እንዲህ አለው፤
4 “ሂድና ለባሪያዬ ለዳዊት እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤ እኔ የምኖርበትን ቤት የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም።