1 አብያ እንደ አባቶቹ ሁሉ አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ፤ ልጁም አሳ በእርሱ ፈንታ ነገሠ፤ በዘመኑም በምድሪቱ ለዐሥር ዓመት ሰላም ሆነ።
2 አሳ በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ቅን የሆነውን ነገር አደረገ፤
3 ባዕዳን መሠዊያዎችንና ማምለኪያ ኰረብታዎችን አስወገደ፤ ማምለኪያ ዐምዶችን አፈረሰ፤ አሼራ ለተባለች ጣዖት አምላክ የቆሙ የዕንጨት ቅርጽ ምስሎችንም ቈራረጠ፤
4 የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን እንዲፈልጉ፣ሕጉንና ትእዛዙንም እንዲፈጽሙ የይሁዳን ሕዝብ አዘዘ።