4 እርሱም በምድር ላይ ወደቀ፤ በዚያ ጊዜም “ሳውል፤ ሳውል፤ ለምን ታሳድደኛለህ?” የሚል ድምፅ ሰማ።
5 ሳውልም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ ማን ነህ?” አለው።እርሱም እንዲህ አለው፤ “እኔማ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ።
6 አሁንም ተነሥተህ ወደ ከተማዪቱ ግባ፤ ማድረግ የሚገባህም ይነገርሃል።”
7 ከሳውል ጋር ይጓዙ የነበሩትም ሰዎች ድምፁን እየሰሙ ማንንም ባላዩ ጊዜ፣ አፋቸውን ይዘው ቆሙ።
8 ሳውልም ከወደቀበት ተነሥቶ ዐይኑን ሲገልጥ ምንም ማየት አልቻለም፤ ስለዚህ ሰዎቹ እጁን ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ አስገቡት።
9 ሦስት ቀንም ታወረ፤ እህል ውሃም አልቀመሰም።
10 በደማስቆ ሐናንያ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤ ጌታም በራእይ፣ “ሐናንያ” ብሎ ጠራው።እርሱም፣ “ጌታ ሆይ፤ እነሆኝ” አለ።