1 ዜና መዋዕል 11:1-7 NASV

1 እስራኤል ሁሉ በኬብሮን ወደ ዳዊት መጥተው እንዲህ አሉት፤ “እነሆ፤ እኛ የገዛ ሥጋህና ደምህ ነን፤

2 በቀደመው ዘመን ሳኦል ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን ወደ ጦርነት የምትመራ አንተ ነበርህ፤ እግዚአብሔር አምላክህም፣ ‘ሕዝቤን እስራኤልን የምትጠብቅ አንተ ነህ፤ ንጉሣቸውም ትሆናለህ’ ብሎሃል”።

3 የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ ንጉሥ ዳዊት ወዳለበት ወደ ኬብሮን መጡ፤ ዳዊትም በኬብሮን በእግዚአብሔር ፊት ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገባ። እግዚአብሔር በሳሙኤል አማካይነት በሰጠው ተስፋ መሠረት ዳዊትን ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት።

4 ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ ኢያቡስ ወደምትባለው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ። በዚያም የሚኖሩ ኢያቡሳውያን

5 ዳዊትን “ወደዚህ ፈጽሞ አትገባም” አሉት፤ ዳዊት ግን የጽዮንን ምሽግ ያዘ፤ እርሷም የዳዊት ከተማ ናት።

6 ዳዊትም፣ “ኢያቡሳዊያንን ቀድሞ የሚወጋ ሰው የሰራዊቱ አዛዥ ይሆናል” አለ፤ ስለዚህ የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ በመጀመሪያ ወጣ፤ እርሱም አዛዥ ለመሆን በቃ።

7 ከዚያም ዳዊት መኖሪያውን በዐምባዪቱ ውስጥ አደረገ፤ ከዚህም የተነሣ የዳዊት ከተማ ተባለች።