21 ከሦስቱ አንዱ ሆኖ ባይቈጠርም እንኳ፣ እጥፍ ክብር አገኘ፤ አዛዣቸውም ሆነ።
22 ከቀብስኤል የመጣውና ታላቅ ጀብዱ የሠራው የዮዳሄ ልጅ በናያስ ብርቱ ተዋጊ ነበረ። እርሱም እጅግ የታወቁ ሁለት የሞአብ ሰዎችን ገደለ። እንዲያውም አንድ ጊዜ በረዶ ምድርን በሸፈነበት ቀን ወደ አንድ ጒድጓድ ወርዶ አንበሳ ገደለ።
23 ደግሞም ቁመቱ አምስት ክንድ የሆነ አንድ ግብፃዊ ገደለ፤ ግብፃዊው የሸማኔ መጠቅለያ የመሰለ ጦር በእጁ ቢይዝም፣ በናያስ ግን ቆመጥ ይዞ ገጠመው፤ ከግብፃዊው እጅ ጦሩን ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደለው።
24 የዮዳሄ ልጅ በናያስ የፈጸመው ጀብዱ ይህ ነበር፤ እርሱም እንደ ሦስቱ ኀያላን ዝነኛ ሆነ።
25 ከሠላሳዎቹም ይልቅ የበለጠ ክብር ተጐናጸፈ፤ ይሁን እንጂ ክሦስቱ አንዱ አልነበረም፤ ዳዊትም የክብር ዘቡ አዣዥ አደረገው።
26 ኀያላኑም እነዚህ ነበሩ፤የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፣የቤተ ልሔሙ የዱዲ ልጅ ኤልያናን፣
27 ሃሮራዊው ሳሞት፣ፊሎናዊው ሴሌድ፣