17 ስለዚህ ሌዋውያኑ የኢዮኤልን ልጅ ኤማንን ሾሙ፤ ከወንድሞቹም የበራክያን ልጅ አሳፍን፣ ከወንድሞቻቸው ከሜራሪ ዘሮች የቂሳን ልጅ ኤታንን ሾሙ፤
18 ከእነርሱም ጋር ወንድሞቻቸው በደረጃ ተሾሙ፤ እነርሱም ዘካርያስ፣ ያዝኤል፣ ሰሚራሞት፣ ይሒኤል፣ ዑኒን፣ ኤልያብ፣ በናያስ፣ መዕሤያን፣ መቲትያ፣ ኤሊፍሌሁ፣ ሚቅኔያ፣ ደግሞም በር ጠባቂዎቹ ዖቤድኤዶምና ይዒኤል ነበሩ።
19 መዘምራኑ ኤማን፣ አሳፍና ኤታን በናስ ጸናጽል ድምፁን ከፍ አድርገው እንዲያሰሙ ተሾሙ፤
20 ዘካርያስ፣ ዓዝኤል፣ ሰሚራሞት፣ ይሒኤል፣ ዑኒ፣ ኤልያብ፣ መዕሤያና በናያስ ደግሞ በአላሞት ቅኝት መሰንቆ ይገርፉ ነበር።
21 እንዲሁም መቲትያ፣ ኤሊፍሌሁ፣ ሚቅኔያ፣ ዖቤድኤዶም፣ ይዒኤል፣ ዓዛዝያ፣ በሺሚኒት ቅኝት በገና ይደረድሩ ነበር።
22 የዝማሬው ኀላፊ ሌዋዊው አለቃ ክናንያ ነበረ፤ ይህን ኀላፊነት የወሰደው በዝማሬ የተካነ ስለ ነበር ነው።
23 በራክያና ሕልቃና የታቦቱ በር ጠባቂዎች ነበሩ፤