29 ለስሙ የሚገባውን ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤መባ ይዛችሁ በፊቱ ቅረቡ፤በቅድስናውም ክብር ለእግዚአብሔር ስገዱ።
30 ምድር ሁሉ በፊቱ ትንቀጥቀጥ፤ዓለም በጽኑ ተመሥርታለች፤ አትናወጥምም።
31 ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድር ሐሤት ታድርግ፤በአሕዛብም መካከል፤ “እግዚአብሔር ነገሠ!” ይበሉ።
32 ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ ይናወጥ፤ሜዳዎችና በእርሷ ላይ ያሉ ሁሉ ሐሤት ያድርጉ።
33 ያን ጊዜ የዱር ዛፎች በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይላቸዋል፤በደስታ ይዘምራሉ፤በምድረ በዳ ላይ ሊፈርድ ይመጣልና።
34 ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
35 “አዳኛችን እግዚአብሔር ሆይ ታደገን፤ለቅዱስ ስምህ ምስጋና እንድናቀርብ፣ በምስጋናህም እንድንከብር ሰብስበን፤ከአሕዛብም መካከል ታደገን”ብላችሁ ጩኹ።