1 የእስራኤል ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፣
2 ዳን፣ ዮሴፍ፣ ብንያም፣ ንፍታሌም፣ ጋድ፣ አሴር።
3 የይሁዳ ወንዶች ልጆች፤ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፤ እነዚህን ሦስቱን ከከነዓናዊት ሚስቱ ከሴዋ ወለደ። የበኵር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ሆነ፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው።
4 የልጁም ሚስት የነበረችው ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ ይሁዳም ባጠቃላይ አምስት ወንዶች ልጆች ነበሩት።
5 የፋሬስ ወንዶች ልጆች፤ኤስሮም፣ ሐሙል።
6 የዛራ ወንዶች ልጆች፤ዘምሪ፣ ኤታን፣ ሄማን፣ ከልኮል፣ ዳራ፤ ባጠቃላይ አምስት ናቸው።