47 የያህዳይ ወንዶች ልጆች፤ሬጌም፣ ኢዮታም፣ ጌሻን፣ ፋሌጥ፣ ዔፋ፣ ሸዓፍ።
48 የካሌብ ቁባት ማዕካ ሼቤርን፣ ቲርሐናን ወለደችለት።
49 እንዲሁም የመድማናን አባት ሸዓፍን፣ የመክቢናንና የጊብዓን አባት ሱሳን ወለደች። ካሌብ ዓክሳ የተባለች ልጅ ነበረችው።
50 እነዚህ ሁሉ የካሌብ ዘሮች ነበሩ።የኤፍራታ የበኵር ልጅ የሑር ወንዶች ልጆች፤ሦባል የቂርያትይዓሪም አባት፤
51 ሰልሞን የቤተ ልሔም አባት፤ ሐሬፍ የቤት ጋዴር አባት።
52 የቂርያትይዓሪም አባት የሦባል ዘሮች፤የመናሕታውያን ነዋሪዎች እኵሌታ፣ ሀሮኤ፤
53 እንዲሁም የቂርያትይዓሪም ጐሣዎች፤ ይትራውያን፣ ፉታውያን፣ ሹማታውያን፣ ሚሽራውያን፣ ጾርዓውያንና ኤሽታኦላውያን ከእነዚህ የመጡ ጐሣዎች ነበሩ።