6 ዳዊትም ሌዋውያኑን በሌዊ ልጆች በጌድሶን፣ በቀዓትና በሜራሪ በየጐሣቸው መደባቸው።
7 ከጌድሶናውያን ወገን፤ለአዳን፣ ሰሜኢ።
8 የለአዳን ወንዶች ልጆች፤የመጀመሪያው ይሒኤል፣ ዜቶም፣ ኢዮኤል፤ ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።
9 የሰሜኢ ወንዶች ልጆች፤ሰሎሚት፣ ሐዝኤል፣ ሐራን፤ ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።እነዚህ የለአዳን ቤተ ሰብ አለቆች ናቸው።
10 የሰሜኢ ወንዶች ልጆች፤ኢኢት፣ ዚዛ፣ የዑስ፣ በሪዓ፤ እነዚህአራቱ የሰሜኢ ልጆች ናቸው።
11 የመጀመሪያው ኢኢት፣ ሁለተኛው ደግሞ ዚዛ ነበረ፤ የዑስና በሪዓ ግን ብዙ ወንዶች ልጆች አልነበሯቸውም፤ ስለዚህ የተቈጠሩት በሥራ መደብ እንደ አንድ ቤተ ሰብ ሆነው ነው።
12 የቀዓት ወንዶች ልጆች፤እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል፤ ባጠቃላይ አራት ናቸው።