1 የቤተ መቅደሱ በር ጠባቂዎች አመዳደብ፤ከቆሬያውያን ወገን፤ ከአሳፍ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነው የቆሬ ወንድ ልጅ ሜሱላም።
2 ሜሱላም ወንዶች ልጆች ነበሩት፤የመጀመሪያው ዘካሪያስ፣ሁለተኛው ይዲኤል፣ሦስተኛው ዮዛባት፣አራተኛው የትኒኤል፣
3 አምስተኛው ኤላም፣ስድስተኛው ይሆሐናን፣ሰባተኛው ኤሊሆዔናይ።
4 ዖቤድኤዶምም እንደዚሁ ወንዶችልጆች ነበሩት፤የመጀመሪያው ሸማያ፣ሁለተኛው ዮዛባት፣ሦስተኛው ኢዮአስ፣አራተኛው ሣካር፣አምስተኛው ናትናኤል፣
5 ስድስተኛው ዓሚኤል፣ሰባተኛው ይሳኮር፣ስምንተኛው ፒላቲ፤እግዚአብሔር ዖቤድኤዶምን ባርኮታልና።