1 ዳዊት በኬብሮን ሳለ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆም የተወለደው የበኵር ልጁ አምኖን፣ሁለተኛው ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢግያ የተወለደው ዳንኤል፣
2 ሦስተኛው ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም፣አራተኛው የአጊት ልጅ አዶንያስ፣
3 አምስተኛው የአቢጣል ልጅ ሰፋጥያስ፣ስድስተኛው ከሚስቱ ከዔግላ የተወለደው ይትረኃም።
4 እነዚህ ስድስቱ የተወለዱት ዳዊት በኬብሮን ሆኖ ሰባት ዓመት ተኩል በገዛበት ጊዜ ነበር።ዳዊት በኢየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ፤