28 የሳሙኤል ወንዶች ልጆች፤የበኵር ልጁ ኢዮኤል፣ሁለተኛው ልጁ አብያ።
29 የሜራሪ ዘሮች፤ሞሖሊ፣ ልጁ ሎቤኒ፣ልጁ ሰሜኢ፣ ልጁ ዖዛ፣
30 ልጁ ሳምዓ፣ ልጁ ሐግያ፣ልጁ ዓሣያ።
31 ታቦቱ ከገባ በኋላ፣ ዳዊት የመዘምራን አለቃ አድርጎ በእግዚአብሔር ቤት የሾማቸው ሰዎች እነዚህ ናቸው፤
32 እነርሱም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ፣ በማደሪያው ይኸውም በመገናኛው ድንኳን ፊት ሆነው እየዘመሩ ያገለግሉ ነበር፤ አገልግሎታቸውንም የሚያከናውኑት በወጣላቸው ደንብ መሠረት ነው።
33 ከወንዶች ልጆቻቸው ጋር ሆነው ያገለገሉ ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ከቀዓታውያን ልጆች፤ ዘማሪው ኤማን፣ የኢዮኤል ልጅ፣ የሳሙኤል ልጅ፣
34 የሕልቃና ልጅ፣ የይሮሐም ልጅ፣የኤሊኤል ልጅ፣ የቶዋ ልጅ