44 በስተግራቸው በኩል አብረዋቸው ያሉት የሜራሪ ልጆች፤የቂሳ ልጅ ኤታን፣ የአብዲ ልጅ፣የማሎክ ልጅ፣
45 የሐሸብያ ልጅ፣የአሜስያስ ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ፣
46 የአማሲ ልጅ፣ የባኒ ልጅ፣የሴሜር ልጅ፣
47 የሞሖሊ ልጅ፣የሙሲ ልጅ የሜራሪ ልጅ፣የሌዊ ልጅ፣
48 ሌዋውያን ወንድሞቻቸው ግን የእግዚአብሔርን ቤት የማደሪያ ድንኳን ተግባር እንዲያከናውኑ ተመድበው ነበር።
49 የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ባዘዘው መሠረት ስለ እስራኤል ማስተስረያ በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ የሚከናወነውን ተግባር ሁሉ፣ በመሠዊያው ላይ የሚቃጠል መሥዋዕትና በዕጣኑ መሠዊያ ላይ የሚቀርበውን መሥዋዕት የሚያቀርቡት ግን አሮንና ዘሮቹ ብቻ ነበሩ።
50 የአሮን ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ልጁ አልዓዛር፣ ልጁ ፊንሐስ፣ልጁ አቢሱ