1 ዜና መዋዕል 7:2-8 NASV

2 የቶላ ወንዶች ልጆች፤ኦዚ፣ ረፋያ፣ ይሪኤል፣ የሕማይ፣ ይብሣም፣ ሽሙኤል፤ እነዚህ የየቤተ ሰባቸው አለቆች ናቸው፤ በዳዊት ዘመነ መንግሥት ከቶላ ዘሮች፣ በየትውልድ ሐረጋቸው የተቈጠሩት የቶላ ዘሮች ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ ቍጥራቸውም ሃያ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበረ።

3 የኦዚ ወንድ ልጅ፤ይዝረሕያ።የይዝረሕያ ወንዶች ልጆች፤ሚካኤል፣ አብድዩ፣ ኢዩኤል፣ ይሺያ፤ አምስቱም አለቆች ነበሩ።

4 ብዙ ሚስቶችና ልጆች ስለ ነበሩአቸው፣ ከቤተ ሰባቸው የትውልድ ሐረግ ለውጊያ ብቁ የሆኑ ሠላሳ ስድስት ሺህ ሰዎች ነበሩአቸው።

5 ከይሳኮር ጐሣዎች ሁሉ የተመዘገቡት ተዋጊዎች የቤተ ሰቦቹ ትውልድ ቊጥር ባጠቃላይ ሰማንያ ሰባት ሺህ ነበሩ።

6 ሦስቱ የብንያም ወንዶች ልጆች፤ቤላ፣ ቤኬር፣ ይዲኤል።

7 የቤላ ወንዶች ልጆች፤ኤሴቦን፣ ኦዚ፣ ዑዝኤል፣ ኢያሪሙት፣ ዒሪ፤ ባጠቃላይ አምስት ሲሆኑ፣ የቤተ ሰብ አለቆች ናቸው፤ በትውልድ ሐረግ መዝገባቸው ሃያ ሁለት ሺህ ሠላሳ አራት ተዋጊ ሰዎች ተመዝግበዋል።

8 የቤኬር ወንዶች ልጆች፤ዝሚራ፣ ኢዮአስ፣ አልዓዛር፣ ኤልዮዔናይ፣ ዖምሪ፣ ኢያሪሙት፣ አብያ፣ ዓናቶት፣ ዓሌሜት፤ እነዚህ ሁሉ የቤኬር ልጆች ነበሩ።