4 ብዙ ሚስቶችና ልጆች ስለ ነበሩአቸው፣ ከቤተ ሰባቸው የትውልድ ሐረግ ለውጊያ ብቁ የሆኑ ሠላሳ ስድስት ሺህ ሰዎች ነበሩአቸው።
5 ከይሳኮር ጐሣዎች ሁሉ የተመዘገቡት ተዋጊዎች የቤተ ሰቦቹ ትውልድ ቊጥር ባጠቃላይ ሰማንያ ሰባት ሺህ ነበሩ።
6 ሦስቱ የብንያም ወንዶች ልጆች፤ቤላ፣ ቤኬር፣ ይዲኤል።
7 የቤላ ወንዶች ልጆች፤ኤሴቦን፣ ኦዚ፣ ዑዝኤል፣ ኢያሪሙት፣ ዒሪ፤ ባጠቃላይ አምስት ሲሆኑ፣ የቤተ ሰብ አለቆች ናቸው፤ በትውልድ ሐረግ መዝገባቸው ሃያ ሁለት ሺህ ሠላሳ አራት ተዋጊ ሰዎች ተመዝግበዋል።
8 የቤኬር ወንዶች ልጆች፤ዝሚራ፣ ኢዮአስ፣ አልዓዛር፣ ኤልዮዔናይ፣ ዖምሪ፣ ኢያሪሙት፣ አብያ፣ ዓናቶት፣ ዓሌሜት፤ እነዚህ ሁሉ የቤኬር ልጆች ነበሩ።
9 በትውልድ ሐረግ መዝገባቸውም ውስጥ የየቤተ ሰባቸው አለቆችና ሃያ ሺህ ሁለት መቶ ተዋጊዎች ተመዝግበዋል።
10 የይዲኤል ልጅ፤ቢልሐን።የቢልሐን ወንዶች ልጆች፤የዑስ፣ ብንያም፣ ኤሁድ፣ ክንዓና፣ ዜታን፣ ተርሴስ፣ አኪሳኦር፤