4 ከይሁዳ ልጅ፣ ከፋሬስ ዘሮች፣ የባኒ ልጅ፣ የአምሪ ልጅ፣ የዖምሪ ልጅ፣ የዓሚሁድ ልጅ ዑታይ።
5 ከሴሎናውያን፦የበኵር ልጁ ዓሣያና ወንዶች ልጆቹ።
6 ከዛራውያን፦ይዑኤል፤የሕዝቡ ቍጥር ስድስት መቶ ዘጠና ነበረ።ከይሁዳ ነገድ የሰው ቊጥር ስድስት መቶ ዘጠና ነበር።
7 ከብንያማውያን፦የሐስኑአ ልጅ፣ የሆዳይዋ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ ሰሉ።
8 የይሮሐም ልጅ ብኔያ፤ የሚክሪ ልጅ፣ የኦዚ ልጅ ኤላ፤ የይብንያ ልጅ፣ የራጉኤል ልጅ፣ የሰፋጥያ ልጅ ሜሱላም።
9 በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ በተጻፈው መሠረት ከብንያም ነገድ የሕዝቡ ቍጥር ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስድስት ነበረ፤ እነዚህ ሁሉ ወንዶች የቤተ ሰብ አለቆች ነበሩ።
10 ከካህናቱ፦ዮዳኤ፣ ዮአሪብ፣ ያኪን፤