10 በርሜሉንም ከቤተ መቅደሱ በስተ ደቡብ ምሥራቅ ባለው ማዕዘን በቀኝ በኩል አኖረው።
11 እንዲሁም ምንቸቱን፣ መጫሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን ሠራ። ኪራምም ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች ለንጉሥ ሰሎሞን ሠርቶ ጨረሰ፤ እነዚህም
12 ሁለቱ ዐምዶች፣በአዕማዱ ጫፍ ላይ ያሉት ሁለት ባለ ሳሕን ቅርጽ ጒልላት በዐምዶቹ ላይ ያሉትን ሁለቱን፣ባለ ሳሕን ቅርጽ ጒልላት የሚያስጌጡ ሁለት ዙር መርበቦች፤
13 በዐምዶቹ ላይ ያሉትን ሁለቱን፣ ባለ ሳሕን ቅርጽ ጒልላት እንዲያስጌጡ ለያንዳንዱ መርበብ ሁለት ዙር ሮማኖች ለሁለቱም ዙር መርበቦች በድምሩ አራት መቶ ሮማኖች፤
14 መቆሚያዎች ከነመታጠቢያ ሳሕኖቻቸው፤
15 በርሜሉና እርሱን የተሸከሙት ዐሥራ ሁለት ኮርማዎች፤
16 ምንቸቶችና መጫሪያዎች፣ሜንጦዎችና ከነዚሁም ጋር የተያያዙ ዕቃዎች።ኪራምአቢ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ እንዲሆን ለሰሎሞን የሠራቸው ዕቃዎች በሙሉ ከተወለወለ ናስ የተሠሩ ነበሩ።