1 ከዚያም ሰሎሞን እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ጥቅጥቅ ባለ ደመና ውስጥ እንደሚኖር ተናግሮአል፤
2 እኔም አንተ ለዘላለም ትኖርበት ዘንድ፣ ይህን ታላቅና ድንቅ ቤተ መቅደስ ሠራሁልህ።”
3 መላው የእስራኤል ጉባኤ እዚያው ቆመው ሳሉ፣ ንጉሡ ዘወር ብሎ ባረካቸው፤
4 እንዲህም አለ፤“ለአባቴ ለዳዊት በቃሉ የሰጠውን ተስፋ በእጁ የፈጸመ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ እንዲህ ብሏልና፤