5 እርሱም ሁሉን የሚገዛ አምላክ እግዚአብሔር፣የሚታወቅበት ስሙም እግዚአብሔር ነው።
6 ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤ፍቅርንና ፍትሕን ጠብቅ፤ዘወትርም በአምላክህ ታመን።
7 ነጋዴው በሐሰተኛ ሚዛን ይሸጣል፤ማጭበርበርንም ይወዳል።
8 ኤፍሬም እንዲህ እያለ ይታበያል፤“እኔ ባለጠጋ ነኝ፤ ሀብታምም ሆኛለሁ፤ይህ ሁሉ ሀብት እያለኝ፣ምንም ዐይነት በደል ወይም ኀጢአት አያገኙብኝም።”
9 “ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ፣ አምላካችሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤በዓመት በዓላችሁ ቀን ታደርጉ እንደ ነበረው ሁሉ፣እንደ ገና በድንኳኖች እንድትቀመጡአደርጋችኋለሁ።
10 ለነቢያት ተናገርሁ፤ራእይንም አበዛሁላቸው፤በእነርሱም በኩል በምሳሌ ተናገርሁ።
11 ገለዓድ ክፉ ነው፤ሕዝቡም ከንቱ ናቸው፤ኮርማዎችን በጌልገላ ይሠዋሉን?መሠዊያዎቻቸው በታረሰ መሬት ላይ እንዳለ፣የድንጋይ ክምር ይሆናሉ።