ሆሴዕ 2:2-8 NASV

2 “እናታችሁን ምከሯት፤ ምከሯት፤እርሷ ሚስቴ አይደለችም፤እኔም ባሏ አይደለሁምና።ከፊቷ የዘማዊነት አስተያየትን፣ከጡቶቿም መካከል ምንዝርናዋን ታስወግድ።

3 አለበለዚያ ገፍፌ ዕርቃኗን አስቀራታለሁ፤እንደ ተወለደችበትም ቀን አደርጋታለሁ፤እንደ ምድረ በዳ፣እንደ ደረቅም ምድር አደርጋታለሁ፤በውሃ ጥምም እገድላታለሁ።

4 ለልጆቿ አልራራላቸውም፤የምንዝርና ልጆች ናቸውና።

5 እናታቸው አመንዝራ ነች፤በውርደትም ፀንሳቸዋለች፤እርሷም፣ ‘እንጀራዬንና ውሃዬን ይሰጡኛል፤ሱፌንና የሐር ልብሴን፣ ዘይቴንና መጠጤን ይሰጡኛል፤ስለዚህ ውሽሞቼን ተከትዬ እሄዳለሁ’ አለች።

6 በዚህ ምክንያት መንገዷን በእሾህ እዘጋለሁ፤መውጫ መንገድ እንዳታገኝም ዙሪያዋን በግንብ አጥራለሁ።

7 ውሽሞቿን ተከትላ ትሄዳለች፤ ነገር ግን አትደርስባቸውም፤ትፈልጋቸዋለች፤ ሆኖም አታገኛቸውም።ከዚያም እንዲህ ትላለች፤‘ወደ ቀድሞ ባሌ እመለሳለሁ፤የፊተኛው ኑሮዬ ከአሁኑ ይሻለኛልና።’

8 እርሷም እህል፣ ዘይትና አዲስ የወይን ጠጅ የሰጠኋት፣ለበኣል አምልኮ ያደረጉትን፣ብርንና ወርቅን ያበዛሁላት፣እኔ እንደሆንሁ አላወቀችም።