4 ለልጆቿ አልራራላቸውም፤የምንዝርና ልጆች ናቸውና።
5 እናታቸው አመንዝራ ነች፤በውርደትም ፀንሳቸዋለች፤እርሷም፣ ‘እንጀራዬንና ውሃዬን ይሰጡኛል፤ሱፌንና የሐር ልብሴን፣ ዘይቴንና መጠጤን ይሰጡኛል፤ስለዚህ ውሽሞቼን ተከትዬ እሄዳለሁ’ አለች።
6 በዚህ ምክንያት መንገዷን በእሾህ እዘጋለሁ፤መውጫ መንገድ እንዳታገኝም ዙሪያዋን በግንብ አጥራለሁ።
7 ውሽሞቿን ተከትላ ትሄዳለች፤ ነገር ግን አትደርስባቸውም፤ትፈልጋቸዋለች፤ ሆኖም አታገኛቸውም።ከዚያም እንዲህ ትላለች፤‘ወደ ቀድሞ ባሌ እመለሳለሁ፤የፊተኛው ኑሮዬ ከአሁኑ ይሻለኛልና።’
8 እርሷም እህል፣ ዘይትና አዲስ የወይን ጠጅ የሰጠኋት፣ለበኣል አምልኮ ያደረጉትን፣ብርንና ወርቅን ያበዛሁላት፣እኔ እንደሆንሁ አላወቀችም።
9 “ስለዚህ እህሌን በመከር ጊዜ፣አዲሱም የወይን ጠጅ በደረሰ ጊዜ እወስዳለሁ፤ዕርቃኗንም እንዳትሸፍንበት፣ሱፍና የሐር ልብሴን መልሼ እወስድባታለሁ።
10 አሁንም በውሽሞቿ ፊት፣ነውሯን እገልጣለሁ፤ከእጄም የሚያድናት የለም።