1 እስራኤል ሆይ፤ ደስ አይበልሽ፤እንደ ሌሎችም ሕዝቦች ሐሤት አታድርጊ፤ለአምላክሽ ታማኝ አልሆንሽምና፤በየእህል ዐውድማውም ላይ፣ለጋለሞታ የሚከፈለውን ዋጋ ወደሻል።
2 የእህል አውድማዎችና የወይን መጭመቂያዎች ሕዝቡን አይመግቡም፤አዲሱም የወይን ጠጅ ይጐድልባቸዋል።
3 በእግዚአብሔር ምድር አይቀመጡም፤ኤፍሬም ወደ ግብፅ ይመለሳል፤የረከሰውንም ምግብ በአሦር ይበላል።
4 የወይን ጠጅን ቍርባን ለእግዚአብሔር አያፈሱም፤መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘውም፤እንዲህ ዐይነቱ መሥዋዕት ለእነርሱ የሐዘንተኞች እንጀራ ይሆንባቸዋል፤የሚበሉትም ሁሉ ይረክሳሉ።ይህ ምግብ ለገዛ ራሳቸው ይሆናል፤ወደ እግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ አይገባም።
5 በእግዚአብሔር የበዓል ቀናት፣በዓመት በዓሎቻችሁም ቀን ምን ታደርጋላችሁ?
6 ከጥፋት ቢያመልጡም እንኳ፣ግብፅ ትሰበስባቸዋለች፤ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች።የብር ሀብታቸውን ዳዋ ያለብሰዋል፤ድንኳኖቻቸውም እሾኽ ይወርሰዋል።