1 በኢየሩሳሌም የነገሠው፣ የዳዊት ልጅ፣ የሰባኪው ቃል፤
2 ሰባኪው፣“ከንቱ፣ ከንቱ፣የከንቱ ከንቱ፤ሁሉም ነገር ከንቱ ነው” ይላል።
3 ከፀሓይ በታች ከሚለፋበት ተግባር ሁሉ፣ሰው ምን ትርፍ ያገኛል?
4 ትውልድ ይሄዳል፤ ትውልድ ይመጣል፤ምድር ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።