1 የሞቱ ዝንቦች ሽቶን እንደሚያገሙ፣ትንሽ ሞኝነትም ጥበብንና ክብርን ያቀላል።
2 የጠቢብ ልብ ወደ ቀኝ፣የሞኝ ልብ ግን ወደ ግራ ያዘነብላል።
3 ሞኝ በጐዳና ሲሄድ ማስተዋል ይጐድለዋል፤ጅል መሆኑንም ለማንም ይገልጻል።
4 የገዥ ቊጣ በተነሣብህ ጊዜ፣ስፍራህን አትልቀቅ፤ትዕግሥት ታላቁን ጥፋት ጸጥ ያደርጋልና።
5 ከፀሓይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፤ይህም ከገዥ የሚወጣ ስሕተት ነው፤
6 ሞኞች በብዙ የክብር ስፍራዎች ሲቀመጡ፣ሀብታሞች ግን በዝቅተኛ ስፍራ ሆነዋል።
7 መሳፍንት እንደ ባሮች በእግራቸው ሲሄዱ፣ባሮች ፈረስ ላይ ተቀምጠው አይቻለሁ።