5 ከፀሓይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፤ይህም ከገዥ የሚወጣ ስሕተት ነው፤
6 ሞኞች በብዙ የክብር ስፍራዎች ሲቀመጡ፣ሀብታሞች ግን በዝቅተኛ ስፍራ ሆነዋል።
7 መሳፍንት እንደ ባሮች በእግራቸው ሲሄዱ፣ባሮች ፈረስ ላይ ተቀምጠው አይቻለሁ።
8 ጒድጓድን የሚምስ ራሱ ይገባበታል፤ቅጥርንም የሚያፈርስ እባብ ይነድፈዋል።
9 ድንጋይ የሚፈነቅል ይጐዳበታል፤ግንድንም የሚፈልጥ አደጋ ላይ መውደቁ አይቀርም።
10 መጥረቢያ ቢደንዝ፣ጫፉም ባይሳል፣ብዙ ጒልበት ይጨርሳል፤ብልኀት ግን ለውጤት ያበቃል።
11 እባብ በድግምት ከመፍዘዙ በፊት ቢነድፍ፣ለደጋሚው ምንም አይጠቅመውም።