1 እንጀራህን በውሃ ላይ ጣል፤ከብዙ ቀን በኋላ መልሰህ ታገኘዋለህና።
2 ሀብትህን ሰባት ቦታ፣ እንዲያውም ስምንት ቦታ ከፍለህ አስቀምጥ፤በምድሪቱ ላይ የሚመጣውን ጥፋት አታውቅምና።
3 ደመናት ውሃ ካዘሉ፣በምድር ላይ ዝናብን ያዘንባሉ፤ዛፍ ወደ ደቡብም ሆነ ወደ ሰሜን ቢወድቅ፣በወደቀበት ቦታ በዚያ ይጋደማል።
4 ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፤ደመናትንም የሚያይ አያጭድም።