13 እግዚአብሔር ያደረገውን ተመልከት፤እርሱ ያጣመመውን፣ማን ሊያቃናው ይችላል?
14 ጊዜው መልካም ሲሆን፣ ደስ ይበልህ፤ጊዜው ክፉ ሲሆን ግን ይህን አስብ፤እግዚአብሔር አንዱን እንዳደረገ፣ሌላውንም አድርጎአል፤ስለዚህ ሰው ስለ ወደ ፊት ሁኔታው፣ምንም ሊያውቅ አይችልም።
15 በዚህ ከንቱ በሆነው ሕይወቴ እነዚህን ሁለቱን ነገሮች አይቻለሁ፤ጻድቅ በጽድቁ ሲጠፋ፣ኀጥእም በክፋቱ ዕድሜው ሲረዝም።
16 እጅግ ጻድቅ፣እጅግም ጠቢብ አትሁን፤ራስህን ለምን ታጠፋለህ?
17 እጅግ ክፉ አትሁን፤ሞኝም አትሁን፤ለምንስ ያለ ቀንህ ትሞታለህ?
18 አንዱን ይዞ ሌላውንም አለመልቀቅ መልካም ነው፤እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውጽንፈኝነትን ያስወግዳል።
19 በአንድ ከተማ ካሉ ዐሥር ገዦች ይልቅ፣ጥበብ ጠቢቡን ሰው ኀያል ታደርገዋለች።