4 የጠቢባን ልብ በሐዘን ቤት ነው፤የሞኞች ልብ ግን በደስታ ቤት ነው።
5 የሞኞችን መዝሙር ከመስማት፣የጠቢባንን ሰዎች ተግሣጽ መስማት ይሻላል።
6 የሰነፎች ሣቅ፣ከድስት ሥር እንደሚንጣጣ የእሾኽ ማገዶ ነው፤ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።
7 ግፍ ጠቢብን ሞኝ ያደርጋል፤ጒቦም ልብን ያበላሻል።
8 የአንድ ነገር ፍጻሜ ከጅማሬው ይሻላል፤ትዕግሥተኛም ከትዕቢተኛ ይሻላል፤
9 የሞኞች ቊጣ በዕቅፋቸው ውስጥ ስለ ሆነ፣በመንፈስህ ለቊጣ አትቸኵል።
10 አንተም፣ “ከእነዚህ ቀናት የቀድሞዎቹ ለምን ተሻሉ?” አትበል፤እንዲህ ያሉትን ጥያቄዎች መጠየቅ ጠቢብነት አይደለምና።