ሚክያስ 3:3-9 NASV

3 የሕዝቤን ሥጋ በላችሁ፤ቈዳቸውን ገፈፋችሁ፤ዐጥንቶቻቸውንም ሰባበራችሁ፤በመጥበሻ እንደሚጠበስ፣በድስት እንደሚቀቀል ሥጋ ቈራረጣችኋቸው።

4 እነርሱም ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ፤እርሱ ግን አይመልስላቸውም፤ካደረጉት ክፋት የተነሣ፣በዚያ ጊዜ ፊቱን ከእነርሱ ይሰውራል።

5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ሕዝቤን የሚያስቱ ነቢያት፣ሰው ሲያበላቸው፣ ‘ሰላም አለ’ ይላሉ፤ሳያበላቸው ሲቀር ግን፣ጦርነት ሊያውጁበት ይነሣሉ።

6 ስለዚህ ሌሊቱ ያለ ራእይ፣ጨለማውም ያለ ንግርት ይመጣባችኋል፤በነቢያት ላይ ፀሐይ ትጠልቅባቸዋለች፤ቀኑም ይጨልምባቸዋል።

7 ባለ ራእዮች ያፍራሉ፤ንግርተኞችም ይዋረዳሉ፤ሁሉም ፊታቸውን ይሸፍናሉ፤ከእግዚአብሔር መልስ የለምና።”

8 እኔ ግን፣ለያዕቆብ በደሉን፣ለእስራኤልም ኀጢአቱን እነግር ዘንድኀይልን፣ በእግዚአብሔር መንፈስ፣ፍትሕና ብርታት ተሞልቻለሁ።

9 እናንት የያዕቆብ ቤት መሪዎች፣እናንት የእስራኤል ቤት ገዦች፣ፍትሕን የምትንቁ፤ትክክለኛ የሆነውንም ነገር ሁሉ የምታጣምሙ፤ ስሙ፤