ሚክያስ 4:1-6 NASV

1 በመጨረሻው ዘመን፣ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተራራ፣ከተራሮች ልቆ ይታያል፤ከኰረብቶች በላይ ከፍ ይላል፤ሕዝቦችም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ።

2 ብዙ አሕዛብ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤“ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንሂድ፤በመንገዱ እንድንሄድ፣መንገዱን ያስተምረናል።”ሕግ ከጽዮን ይመጣል፤ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም።

3 እርሱ በብዙ ሕዝብ መካከል ይፈርዳል፤በሩቅና በቅርብ ባሉ ኀያላን መንግሥታት መካከል ያለውን ግጭት ያቆማል፤ሰይፋቸውን ማረሻ፣ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጉታል።አንዱ መንግሥት በሌላው መንግሥት ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ከእንግዲህም የጦርነት ትምህርት አይማሩም።

4 እያንዳንዱ ሰው በገዛ ወይኑ ሥር፣ከገዛ በለሱም ሥር ይቀመጣል፤የሚያስፈራቸው አይኖርም፤ የእግዚአብሔር ጸባኦት አፍ ተናግሮአልና።

5 አሕዛብ ሁሉ፣በአማልክቶቻቸው ስም ይሄዳሉ፤እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም፣ከዘላለም እስከ ዘላለም እንሄዳለን።

6 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በዚያች ቀን ሽባውን እሰበስባለሁ፤ስደተኞችንና ለሐዘን ያደረግኋቸውን፣ወደ አንድ ቦታ አመጣለሁ።