ሚክያስ 4:4-10 NASV

4 እያንዳንዱ ሰው በገዛ ወይኑ ሥር፣ከገዛ በለሱም ሥር ይቀመጣል፤የሚያስፈራቸው አይኖርም፤ የእግዚአብሔር ጸባኦት አፍ ተናግሮአልና።

5 አሕዛብ ሁሉ፣በአማልክቶቻቸው ስም ይሄዳሉ፤እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም፣ከዘላለም እስከ ዘላለም እንሄዳለን።

6 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በዚያች ቀን ሽባውን እሰበስባለሁ፤ስደተኞችንና ለሐዘን ያደረግኋቸውን፣ወደ አንድ ቦታ አመጣለሁ።

7 የሽባዎችን ትሩፍ፣የተገፉትንም ብርቱ ሕዝብ አደርጋለሁ፤ከዚያች ቀን አንሥቶ እስከ ዘላለም፣ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ በእነርሱ ላይ ይነግሣል።

8 አንተ የመንጋው መጠበቂያ ማማ ሆይ፤የጽዮን ሴት ልጅ ዐምባ ሆይ፤የቀድሞው ግዛትህ ይመለስልሃል፤የመንግሥትም ሥልጣን ለኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ይሆናል።”

9 አሁንስ እንደዚህ የምትጮኺው ለምንድን ነው?ንጉሥ የለሽምን?ምጥ እንደ ያዛት ሴት የተጨነቅሽው፣መካሪሽ ስለ ጠፋ ነውን?

10 የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፤ምጥ እንደ ያዛት ሴት ተጨነቂ፤አሁንስ ከከተማ ወጥተሽ፣በሜዳ ላይ መስፈር አለብሽና፤ወደ ባቢሎን ትሄጃለሽ፣በዚያ ከጠላት እጅ ትድኛለሽ፤ እግዚአብሔር በዚያ፣ከጠላቶችሽ ይታደግሻል።