ሚክያስ 7:4-10 NASV

4 ከእነርሱ ይሻላል የተባለው እንደ አሜከላ፣እጅግ ቀና የተባለውም እንደ ኵርንችት ነው፤የጠባቂዎቻችሁ ቀን ደርሶአል፤የእግዚአብሔር የፍርድ ቀን መጥቶአል፤የሚሸበሩበትም ጊዜ አሁን ደርሶአል።

5 ባልንጀራህን አትመን፤በጓደኛህም አትታመን፤በዕቅፍህ ለምትተኛዋ እንኳ፣ስለምትነግራት ቃል ተጠንቀቅ።

6 ወንድ ልጅ አባቱን ይንቃል፤ሴት ልጅ በእናቷ ላይ፤ምራት በአማቷ ላይ ትነሣለች፤የሰው ጠላቶች የገዛ ቤተ ሰዎቹ ናቸውና።

7 እኔ ግን እግዚአብሔርን ተስፋ አደርጋለሁ፤አዳኜ የሆነውን አምላክ እጠብቃለሁ፤አምላኬ ይሰማኛል።

8 ጠላቴ ሆይ፤ በእኔ ላይ በደረሰው ደስ አይበልሽ!ብወድቅም እንኳ እነሣለሁ፤በጨለማ ብቀመጥ እንኳ፣ እግዚአብሔር ብርሃኔ ይሆናል።

9 እርሱን ስለ በደልሁ፣እስኪቆምልኝእስኪፈርድልኝም ድረስ፣ የእግዚአብሔርን ቊጣ እቀበላለሁ፤እርሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል፤እኔም ጽድቁን አያለሁ።

10 ጠላቴም ታያለች፤ኀፍረትንም ትከናነባለች፤“አምላክህ እግዚአብሔር የት አለ?”ያለችኝን፣ዐይኖቼ ውድቀቷን ያያሉ፤አሁንም እንኳ፣እንደ መንገድ ጭቃ ትረገጣለች።