ሶፎንያስ
ምዕራፎች 1:5-11
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
5የሰማይን ሰራዊት ለማምለክ፣በሰገነት ላይ ወጥተው የሚሰግዱትን፣ ለእግዚአብሔር እየሰገዱ፣ በስሙም እየማሉ፣በሚልኮምም ደግሞ የሚምሉትን፣
6 እግዚአብሔርን ከመከተል ወደ ኋላ የሚመለሱትን፣እግዚአብሔርን የማይፈልጉትን፣ እንዲረዳቸውም የማይጠይቁትን አጠፋለሁ።
7በልዑል እግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ፤የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና። እግዚአብሔር መሥዋዕት አዘጋጅቶአል፤የጠራቸውንም ቀድሶአል።
8 በእግዚአብሔር የመሥዋዕት ቀን፣መሳፍንቱንና የንጉሡን ልጆች፣እንግዳ ልብስ የሚለብሱትን ሁሉ እቀጣለሁ።
9በዚያን ቀን፣በመድረኩ ላይ የሚዘሉትን ሁሉ፣የአማልክቶቻቸውን ቤት፣በዐመፅና በማጭበርበር የሚሞሉትን እቀጣለሁ።
10 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በዚያ ቀን ‘ከዓሣ በር’ ጩኸትበሁለተኛው አደባባይ ዋይታ፣ከኰረብቶችም ታላቅ ሽብር ይሰማል።
11እናንት በመክቴሽ ገበያ የምትኖሩ ዋይ በሉ፤ነጋዴዎቻችሁ ሁሉ ይደመሰሳሉ፤በብር የሚነግዱትም ሁሉ ይሞታሉ።