ሶፎንያስ 1:6-12 NASV

6 እግዚአብሔርን ከመከተል ወደ ኋላ የሚመለሱትን፣እግዚአብሔርን የማይፈልጉትን፣ እንዲረዳቸውም የማይጠይቁትን አጠፋለሁ።

7 በልዑል እግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ፤የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና። እግዚአብሔር መሥዋዕት አዘጋጅቶአል፤የጠራቸውንም ቀድሶአል።

8 በእግዚአብሔር የመሥዋዕት ቀን፣መሳፍንቱንና የንጉሡን ልጆች፣እንግዳ ልብስ የሚለብሱትን ሁሉ እቀጣለሁ።

9 በዚያን ቀን፣በመድረኩ ላይ የሚዘሉትን ሁሉ፣የአማልክቶቻቸውን ቤት፣በዐመፅና በማጭበርበር የሚሞሉትን እቀጣለሁ።

10 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በዚያ ቀን ‘ከዓሣ በር’ ጩኸትበሁለተኛው አደባባይ ዋይታ፣ከኰረብቶችም ታላቅ ሽብር ይሰማል።

11 እናንት በመክቴሽ ገበያ የምትኖሩ ዋይ በሉ፤ነጋዴዎቻችሁ ሁሉ ይደመሰሳሉ፤በብር የሚነግዱትም ሁሉ ይሞታሉ።

12 በዚያ ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ተንደላቀው የሚኖሩትን፣በዝቃጩ ላይ እንደ ቀረ የወይን ጠጅ የሆኑትን፣‘ክፉም ይሁን መልካም፣ እግዚአብሔር ምንም አያደርግም’ የሚሉትን ቸልተኞች እቀጣለሁ።