1 እናንት ዕረፍት የሌላችሁ ሕዝብ ሆይ፤በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ተከማቹም፤
2 የተወሰነው ጊዜ ሳይደርስ፣ቀኑ እንደ ገለባ ሳይጠራርጋችሁ፣ የእግዚአብሔር ጽኑ ቊጣ በእናንተ ላይ ሳይመጣ፣ የእግዚአብሔር የመዓት ቀንሳይደርስባችሁ ተሰብሰቡ።
3 እናንት የምድር ትሑታን ሁሉ፣ትእዛዙን የምትፈጽሙ፣ እግዚአብሔርን እሹ፤ጽድቅንና ትሕትናን ፈልጉ፤ በእግዚአብሔር የቊጣ ቀን፣ትሰወሩ ይሆናል።
4 ጋዛ ባድማ ትሆናለች፤አስቀሎናም ፈራርሳ ትቀራለች፤አዛጦን በቀትር ባዶ ትሆናለች፤አቃሮንም ትነቀላለች።
5 እናንት በባሕር ዳርቻ የምትኖሩ፣የከሊታውያን ሰዎች ሆይ፤ ወዮላችሁየፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፤በአንቺ ላይ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤“ፍጹም አጠፋሻለሁ፤ከነዋሪዎችሽም የሚተርፍ የለም።”
6 የቀርጤስ ሰዎች የሚኖሩበት በባሕሩዳር ያለው ምድር፣የእረኞች መኖሪያና የበጎች በረት ይሆናል፤
7 ይህም ለይሁዳ ቤት ትሩፍ ይሰጣል፤እነርሱም በዚያ መሰማሪያ ያገኛሉ።በአስቀሎና ቤቶች ውስጥም፣በምሽት ይተኛሉ፤አምላካቸው እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል፤ምርኮአቸውንም ይመልስላቸዋል።