ሶፎንያስ 2:3-9 NASV

3 እናንት የምድር ትሑታን ሁሉ፣ትእዛዙን የምትፈጽሙ፣ እግዚአብሔርን እሹ፤ጽድቅንና ትሕትናን ፈልጉ፤ በእግዚአብሔር የቊጣ ቀን፣ትሰወሩ ይሆናል።

4 ጋዛ ባድማ ትሆናለች፤አስቀሎናም ፈራርሳ ትቀራለች፤አዛጦን በቀትር ባዶ ትሆናለች፤አቃሮንም ትነቀላለች።

5 እናንት በባሕር ዳርቻ የምትኖሩ፣የከሊታውያን ሰዎች ሆይ፤ ወዮላችሁየፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፤በአንቺ ላይ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤“ፍጹም አጠፋሻለሁ፤ከነዋሪዎችሽም የሚተርፍ የለም።”

6 የቀርጤስ ሰዎች የሚኖሩበት በባሕሩዳር ያለው ምድር፣የእረኞች መኖሪያና የበጎች በረት ይሆናል፤

7 ይህም ለይሁዳ ቤት ትሩፍ ይሰጣል፤እነርሱም በዚያ መሰማሪያ ያገኛሉ።በአስቀሎና ቤቶች ውስጥም፣በምሽት ይተኛሉ፤አምላካቸው እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል፤ምርኮአቸውንም ይመልስላቸዋል።

8 “የሞዓብን ስድብ፣የአሞናውያንንም ፌዝ ሰምቻለሁ፤ሕዝቤን ሰድበዋል፤በምድራቸውም ላይ ዝተዋል።

9 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በሕያውነቴ እምላለሁሞዓብ እንደ ሰዶም፣አሞናውያን እንደ ገሞራ፣ዐረም እንደ ዋጠው ቦታና እንደ ጨውጒድጓድ ለዘላለም ጠፍ ይሆናሉ።ከሕዝቤ የቀሩት ይዘርፏቸዋል፤ከወገኔ የተረፉትም ምድራቸውንይወርሳሉ።”